በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ከፍተኛ አፈፃጸም ላስመዘገቡ የጤና ተቋማት እና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ተሰጠ

You are currently viewing በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ከፍተኛ አፈፃጸም ላስመዘገቡ የጤና ተቋማት እና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ተሰጠ

AMN – መጋቢት 9/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በስሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ግማሽ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ እዉቅና ሰጥቷል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፣ የቢሮ እና የሁሉም ሆስፒታል እንዲሁም የክፍለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

እውቅናው የቢኤስሲ፣ የሪፎርም ስራዎች እንዲሁም የተለያዩ የኢኒሼቲቭ አፈፃፀሞች እና አገልግሎት አሰጣጥን መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ ይህንን ባማከለ መልኩ ተቋማት ባላቸው አፈፃፀም ውጤት መሰጠቱም ተመላክቷል።

በእዉቅና አሰጣጥ መርሀ ግብሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፣ ጤና ተቋማቱ ባላቸው አፈጻፀም እዉቅና መሰጠቱ የተሻለ መነሳሳት የሚፈጥር እና የሚፈለገዉን አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

በምዘናው ወቅት የታዩ ውስንነቶችን በቀሪ ጊዜያት ለማሻሻል እንደሚረዳም ተናግረዋል።

ጤና አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር በሆስፒታሎችም ሆነ በክፋለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት የተሻለ አፈጻፀም እንዳለ እና በቀጠይ ይበልጥ መስራት እንደሚገባም ዶክተር ዮሐንስ አሳስበዋል።

በአጠቃላይ በተደረገው የ6ወር አፈጻፀም ምዘና ካሉት 6 ሆስፒታሎች፣ ዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል፣ ራስ ደስታ መታሰቢያ ሆስፒታል እና ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከክፍለ ከተሞች ደግሞ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና አራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤቶች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በመውጣት እዉቅና አግኝተዋል።

እንዲሁም ዳግማዊ ምኒልክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቢሮ ስር ላሉ ጤና ተቋማት ያለውን የሰው ሃይል በማብቃት እና ጥናትና ምርምሮችን በመስራት እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋጽኦ ከቢሮው እውቅና እንደተሰጠው የቢሮው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review