በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ አገልግሎትን ሲያዛቡ በነበሩ 1 ሺህ 816 አመራሮች እና ሠራተኞች ላይ ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የቅጣት እርምጃዎችን መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡
ከዚህም ውስጥ 90 የሚሆኑ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል ያሉ ኃላፊዎች ከኃላፊነት እስከ ማንሳት የደረሱ የተለያዩ ቅጣቶች መቀጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
በገቢዎች፣ በመሬት፣ በአሽከርካሪ፣ በእሳት አደጋ፣ በቄራዎች፣ በፓርኮች ኮርፖሬሽን በመሳሰሉት ድርጅቶች፣ ጉቦ በመቀበል አገልግሎትን ሲያዛቡ በነበሩ 1 ሺህ 726 ሠራተኞች ላይም የተለያየ እርምጃ መወሰዱን ከንቲባዋ አንስተዋል፡፡