በመዲናዋ ከተማ አቀፍ የጥናትና ምርምር ውድድር እየተካሄደ ነው

You are currently viewing በመዲናዋ ከተማ አቀፍ የጥናትና ምርምር ውድድር እየተካሄደ ነው

AMN- ሚያዚያ 08/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ “ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ሀሳብ ከተማ አቀፍ የጥናትና ምርምር ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

ጥናትና ምርምሮቹ በከተማዋ ባሉ 14 ኮሌጆችና አንድ የምርታማነትና ልህቀት ማዕከል ሲወዳደሩ ቆይተው ሰባት ጥናቶች ለመጨረሻ ዙር አልፈው ለአሸናፊነት እየተወዳደሩ መሆኑን ውድድሩን በዋናነት እያስተባበረ የሚገኘው የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ ልጋኒ፣ በውድድሩ የሚቀርቡ ሁሉም ጥናቶች ባመጡት ተጨባጭ ችግር ፈቺ የምርምር ውጤት የተመረጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ የሚካሄደው ውድድር አንድ አሸናፊ ጥናት የሚመረጥበት ሲሆን፣ አሸናፊው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው 4ኛው ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክሎ የሚቀርብ እንደሚሆን አቶ መሀመድ ገልፀዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review