በመዲናዋ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታወቀ Post published:May 7, 2025 Post category:መልካም አስተዳደር AMN – ሚያዝያ 29/2017 በመዲናዋ ሲያጋጥሙ የነበሩ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡ በመዲናዋ በመቀናጀት በተሰሩ ስራዎች በአደባባይ የተከበሩ በዓላት እና ኮንፈረንሶች ያለምንም ችግር መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተናግረዋል። ለስራ ምቹ የሆነ፣ ተወዳዳሪና ደረጃውን የሚመጥን ተቋም የመገንባት ስራ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን ስለመከናወኑም ኮሚሽነር ጌቱ አመላክተዋል፡፡ የማህበረሰቡን ሰብዓዊ መብቶች የጠበቀ ህጋዊና አስተዳደራዊ አገልግሎት የመስጠት ስራ በአዲስ አበባ ፓሊስ የተከናወነ እና እየተከናወነ ያለ ተግባር መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ከአፍሪካ አምስት ከተሞች የአዲስ አበባ ፓሊስን በአገልግሎት አሰጣጡ ተጠቃሽ ለማድረግ በቴክኖሎጅ የታገዘ ተቋም መገንባት ላይ በትኩረት ስለመሰራቱ ተጠቅሷል። አዲስ አበባን ከወንጀልና ከፀጥታ ስጋት የፀዳች ከተማ ለማድረግ ተቋሙ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ይገኛሉ። በንጉሱ በቃሉ 0 Reviews ( 0 out of 0 ) Write a Review Submit Review You Might Also Like አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን – አቶ ሞገስ ባልቻ April 15, 2025 ህይወት አድን በጎነት March 22, 2025 የፀጥታ አካላት በእውቀታቸው እና በመስዋዕትነታቸው የኢትዮጵያን ሰላም እንዲያፀኑ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ጥሪ አቀረቡ June 21, 2025