በአፋር ክልል ሚሌ ከተማ ከቦቴ ነዳጅ በመቀሸብ ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ የተደረሰበት ሾፌርና ተቀባይ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዱልቃድር ከጅቡቲ ነዳጅ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ በመንቀሳቀስ ላይ የነበረ አሽከርካሪ እና በግዥ ላይ የነበረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
በእለቱ 49 ሺህ ሊትር ከጫነው የነዳጅ ቦቴ ሁለት ሺህ ሊትር በመቀሸብ በግብይት ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አቶ አህመድ ገልጸዋል።