በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እየተመዘገበ ያለው ስኬት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

You are currently viewing በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እየተመዘገበ ያለው ስኬት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

AMN – ሚያዝያ 5/2017

በኢትዮጵያ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እየተመዘገበ ያለው ስኬት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች አፈጻጸም አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የዘንድሮው አመት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተደረገበት በመሆኑ ከሌሎቹ አመታት ለየት ያለ መሆኑን ገልጸዋል።

የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር ረገድ ጥሩ ውጤት መመዝገቡን እና ካለፉት ወራት የቀነሰበት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ የገቢ አቅምን ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ በላይ አጠናከሮ መቀጠል እንደሚገባ በመድረኩ መነሳቱን አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የመንግስት የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም በከፍተኛ ሁኔታ እድገት አስመዝግቧል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review