በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

መንግሥት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 43 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

ሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያ ዲፕሎማቶችን በማሠማራት ባደረገው ጥረት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

በተያያዘ መንግሥት ጃፓን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

መንግሥት በዚሁ አጋጣሚ በድጋሚ ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወዳልተፈጸመባቸው አሀራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ያሳስባል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review