በረመዳን ወቅት እየታየ ያለው የጋራ የኢፍጣር ስነ ስርዓት ኢትዮጵያ ያላትን ብዝሃነት እና አብሮነት የሚያጎለብት ተግባር ነው- ዶክተር ዘላለም ሙላቱ

You are currently viewing በረመዳን ወቅት እየታየ ያለው የጋራ የኢፍጣር ስነ ስርዓት ኢትዮጵያ ያላትን ብዝሃነት እና አብሮነት የሚያጎለብት ተግባር ነው- ዶክተር ዘላለም ሙላቱ

AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም

በረመዳን ወቅት እየታየ ያለው የጋራ የኢፍጣር ስነ ስርዓት ኢትዮጵያ ያላትን ብዝሃነት እና አብሮነት የሚያጎለብት ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች የጋራ የኢ-ፍጣር መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡

በረመዳን ወቅት እየታየ ያለው የጋራ የኢ-ፍጠር ስነ ስርዓት ኢትዮጵያ ያላትን ብዝሃነት እና አብሮነት የሚያጎለብት ተግባር መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንደዚህ አይነት መርሃ ግብር ትውልዱ እነዚህን እሴቶች የጋራ እንዲያደረጋቸው መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶች ፣ወጣቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽከር፣ ትምህርት ቢሮ ትውልዱን በአብሮነት ለማነጽ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው የኢፍጣር መርሃ ግብሩም ወንድማማችነትን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል፣ መርሃ ግብሩ ለመተዋወቅ እና ለመከባበር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው የትምህርት ማህበረሰቡ የሚተገብራቸው መልካም እሴቶች ትውልዱ ብዝሃነትን አክብሮ እንዲቀጥል መሰረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነውን የአብሮነት እሴት በእጅጉ እንደሚያሳድገው የተናሩት ደግሞ በኢፍጣር መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review