በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

መንግሥት ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት መሠረት ዛሬ በሦስት ቻርተር በረራዎች በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአደጋ ሥጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሳዑዲ አረቢያ እና በተለያዩ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review