በሶማሊያ የባህር ዳርቻ በተፈጸመ ጥቃት የ32 ሰዎች ህይወት አለፈ

You are currently viewing በሶማሊያ የባህር ዳርቻ በተፈጸመ ጥቃት የ32 ሰዎች ህይወት አለፈ
  • Post category:ዓለም

AMN ሀምሌ 27/2016

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ማምሻውን በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 32 ንፁሀን ሲሞቱ 63 ቆስለዋል።

በባህር ዳርቻው በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት ከተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች በተጨማሪ አንድ ወታደር መሞቱን የፖሊስ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ከጥቃት ፈፃሚዎቹ አንዱ ራሱን አጥፍቶ የጠፋ ሲሆን ሌሎች 3 ጥቃት ፈፃሚዎችበጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል።

አንድ ጥቃት ፈፃሚ ደግሞ በህይወት መያዙን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ሀላፊነት የወሰደ አካል የለም።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review