በቀጣናው ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት፡- አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ

You are currently viewing በቀጣናው ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት፡- አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ

AMN- መስከረም 8/2017 ዓ.ም

በቀጣናው ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናገሩ፡፡

የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ሚንስትሮች የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተኪያሄደ ነው፡፡

ሚንስትሮቹ በነገው እለት ይፋ የሚደረገው የኢጋድ ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን ላይ ተወያይተው እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ እያከናወነች ያለውን ስራ በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በቀጣናው ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከየኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ናሲሴ ነገ ይፋ እንደሚሆን ለሚጠበቀው የኢጋድ ዘላቂ የ 10 አመት ማስተር ፕላን ስኬት የቱሪዝም ሚንስቴር በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል::

የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፍኖተ ካርታው ለቀጣናው ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም አቅም መፍጠር ጥረት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፤ ለፍኖተ ካርታው ውጤታማነት አባል ሀገራቱ ዕውቀትና ልምዳቸውን በማጋራት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአለም ቱሪዝም ቀንን በማስመልከት የቱሪዝም ሚንስቴር ከኢጋድ እና UNECA ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያኪያሄደ መሆኑ ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review