በቀጣዮቹ ቀናት በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ይጠበቃል

You are currently viewing በቀጣዮቹ ቀናት በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን አዋሳኝ አካባቢዎች ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ይጠበቃል

AMN- ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም

በቀጣዮቹ ቀናት በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ ኬንያ ከመደበኛው በላይ የሙቀት መጠን የሚመዘገብ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የአየር ሁኔታ መረጃ አገልግሎት (ኢክፓክ) አስታውቋል።

የኢክፓክ የአየር ትንበያ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በሱዳን በርካታ አካባቢዎች በኢትዮጵያ በተለይም የአፋር ክልል በቀጣዮቹ ስምንት ቀናት ከፍተኛ የሙቀት መጠን ሊመዘገብ የሚችል መሆኑን ጠቁሟል።

በደቡብ ሱዳንና ኤርትራ እንዲሁም በሰሜን፣ ምእራብ እና ምስራቅ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ሙቀት የሚኖር ይሆናል።

በጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ዩጋንዳ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ በተመሳሳይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ሙቀት ሊመዘገብ ይችላል የሚል የትንበያ መረጃ ማስነበቡን ኢዜአ ዘግቧል።

በአብዛኛው የኤርትራ ክፍል፣ በጅቡቲ፣ ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ምእራባዊ የኬንያ ክፍል፣ በማእከላዊ እና ሰሜን የሶማሊያ ግዛቶች ከመደበኛው ባላይ ሙቀት እንደሚኖራቸው ተመላክቷል።

በኢትዮጵያ ምእራባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች፣ በሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ በሰሜንና ደቡባዊ ታንዛንያ፣ በኡጋንዳ ምእራባዊ ክፍል እንዲሁም በኬንያ ጠረፋማ አካባቢዎች መጠነኛ ዝናብ እንደሚኖርም ይጠበቃል።

የምስራቅ አፍሪካ የአየር ሁኔታ መረጃ አገልግሎት (ኢክፓክ) የአየር ትንበያና ሌሎች ተያያዥ ወቅታዊ ክስተቶችን በመተንበይና በመተንተን የቅድመ ጥንቃቄ መልእክቶችን በማጋራት ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review