AMN – ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በሰሩት ቅንጅታዊ ስራ ውጤት ማምጣት መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማት እና ማዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።
በቀረበው ሪፖርት በ2016 ዓ.ም አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ(ኢ/ር) እና የመሰረተ ልማት እና ማዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግዛቸው አይካ (ዶ/ር ) በመድረኩ የተገኙ ሲሆን የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በቀረበው ሪፖርት ላይ ሀሳብና አስተያየት እየሰጡ ናቸው።
በመሀመድኑር አሊ