በበጀት ዓመቱ አረንጓዴ ቦታዎችን በማልማት ረገድ ከእቅድ በላይ ማከናወን መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ አረንጓዴ ቦታዎችን በማልማት ረገድ ከእቅድ በላይ ማከናወን መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ

AMN – ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደሩን የ2016 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም አቅርበዋል፡፡

ከንቲባዋ ባቀረቡት ሪፖርትም በበጀት ዓመቱ 75 ሄክታር መሬት ማልማት ተችሏል ብለዋል፡፡

በ5ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 17 ነጥብ 44 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ ሽፋኑን በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታትም የአረንጓዴ ሽፋኑን 30 በመቶ ለማድረስ እንደሚሰራ ከንቲባዋ አብራርተዋል።

የሕንፃ ሕግጋትና የከተማ መዋቅራዊ ፕላንን መሠረት ያደረገ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥን ከማሳደግ አንፃርም ለ32 ሺህ 812 ተገልጋዮች የፕላን ስምምነት ለመስጠት ታቅዶ ለ32 ሺህ 484 መስጠት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የከተማ መዋቅራዊ ፕላንን መሠረት ያደረገ ግንባታ በማከናወን ረገድም ለ14 ሺህ 328 ተገልጋች አዲስ ህንፃዎች እንዲገነቡ ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በሽመልስ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review