በበጀት ዓመቱ 102 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ጥገና ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ነው-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ 102 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ጥገና ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ነው-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

AMN – መስከረም 14/2017 ዓ.ም

በበጀት ዓመቱ 102 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ጥገና ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የጀመረውን የአስፋልት መንገድ ጥገና የዘመቻ ስራ በተለያዩ በርካታ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 102 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ የአስፋልት መንገድ ጥገና ለማከናወን አቅዶ እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን አሁን ላይ በክረምቱ ከባድ ዝናብ ምክንያትና በመንገድ ሀብት አጠቃቀም ጉድለት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸውን መንገዶች በመለየት የጥገና ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የአስፋልት መንገድ ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከጎፋ መብራት ኃይል በቀይ መስቀል ወደ አደይ አበባ የሚያደርሰው መንገድ እንደሚገኝበት የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ በተጨማሪም ከጀርመን ወደ ለቡ መብራት ኃይል፣ ከሲ.ኤም.ሲ የተባበሩት ነዳጅ ማደያ ወደ ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ፣ አየር ጤና አደባባይ፣ ጎፋ መብራት ኃይል እና ሌሎችም አካባቢዎች ላይ በቀንና በምሽት ክፍለ ጊዜ የጥገና ስራዎች መከናወናቸው ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review