በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ነጥብ 4 ቢሊየንብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የለማ መሬት ተላለፈ

You are currently viewing በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ነጥብ 4 ቢሊየንብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የለማ መሬት ተላለፈ
  • Post category:ቢዝነስ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ስምንት ባለሃብቶች የለማ መሬት መተላለፉን የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በመግባት መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ባለሃብቶች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

ፓርኩ ከአማራ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ተመልምለው ለተላኩ ስምንት ባለሃብቶች 35 ነጥብ 58 ሄክታር የለማ መሬት ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ 5 ቢሊየን 422 ሚሊየን 239 ሺ 22 ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡና ለ1 ሺህ 989 ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ 11 ቢሊየን 741 ሚሊየን 817 ሺህ 186 ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል ላስመዘገቡ እና 7 ሺህ 37 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ለሚፈጥሩ 31 የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፕሮጀክቶች 96 ጥብ 6 ሄክታር መሬት መተላለፉ ተጠቁሟል፡፡

ቀሪውን 71 ነጥብ 45 ሔክታር መሬት ደግሞ ለባለሃብቶች ለማስተላለፍ ባለሃብቶች እየተጠበቀ መሆኑን የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ወደ ቡሬ የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ በመግባት መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ኮርፖሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review