AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
ከዘመን መለወጫ ጀምሮ በነበሩት በዓላት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ828 ቢሊዮን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙ ተገለፀ።
ከነሐሴ 30 እስከ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በተከናወኑ ከ145 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች የብር 828,549,614,770 ዝውወር ተፈፅሟል።
በወቅቱ በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከተፈፀመው ግብይት ውስጥ 84 በመቶ ያህሉ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም በገንዘብ ከ696.5 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።