በቤሩት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 164 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ 164 ኢትዮጵያውያ ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ፣ የፌዴራል ፖሊሲ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዬች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሲራጅ ረሽድ አቀባባል አድርገውላቸዋል።

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ብሄራዊ ግብረሃይል ተቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

በዚሁ ግብረሃይል አስተባባሪነት በሊባኖስ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ደህንነታቸው ለአደጋ የተጋለጠ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እየተከናወነ ሲሆን ፥ እስካሁን 758 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሃገርቤት መመለስ እንደተቻለ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review