በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

You are currently viewing በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

AMN – ጥር 24/2017 ዓ.ም

በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የጎረቤት ሀገራት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ ለመታደም ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በጉባኤው መክፈቻ ላይ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

በዛሬው እለትም ከፍተኛ አመራሮች የእንጦጦ ፓርክን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸውም በፓርኩ አስጎብኝዎች ገለጻ እና ማብራሪያ እንደተደረገላቸው ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review