በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢፌዲሪ መንግስት ልዑካን ቡድን የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ዱባይ ይገኛል

You are currently viewing በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢፌዲሪ መንግስት ልዑካን ቡድን የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ዱባይ ይገኛል

AMN – የካቲት 4/2017 ዓ.ም

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የኢፌዲሪ ልዑክ ቡድን በአለም የመንግስታት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዱባይ ይገኛል።

ልዑክ ቡድኑ ዱባይ ዓለም ዓቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ በኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) እና ዲፕሎማቶች አቀባበል ተደርጎለታል::

“Shaping Future Governments” በሚል መሪ ቃል እ.ኤ.አ ከፌብሯሪ 11-13 ቀን 2025 በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ልዑክ በከፍተኛ ደረጃ የሁለትዮሽና ባለ ብዙ ወገን መድረኮች፣ በፓናል ውይይቶች እንዲሁም በጎንዮሽ መስተጋብራዊ ክፍለ ጊዜዎች ላይ ተሳትፎ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል::

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ ውጤታማ ፖሊሲ ማውጣት፣ የዜጎች ተሳትፎ፣ ዘላቂ ልማት፣ የውሃና መስኖ አጠቃቀም እና የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎች የመድረኩ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ የጉባኤው መርሃ ግብር ያሳያል፡፡

በዛሬው እለትም በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ላይ መንግስታዊ የአስተዳደር አቅምን በሚያዳብሩ አለም አቀፋዊ ስጋቶች እና እድሎች ላይ ምክክር የሚያደርግ የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በልኡክ ቡድኑ በመወከል ተሳትፎ ማድረጓን ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review