AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም
በክፍለ ከተማዉ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ስራዎች የውሀ መውረጃ ቱቦዎች እና የጋራ መፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎች በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተመርቀዋል ::
የመሰረት ልማት ስራዎቹ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎባቸዋልም ተብሏል ::
በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ 450 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸዉ መሰረት ልማቶች መሰራታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተናግረዋል ::
ኮምሽኑ በ2017 በጀት ዓመት በ750 ሚሊዮን ብር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እቅድ መያዙንም ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ተናግረዋል ::
በቴዎድሮስ ይሳ