በቦሌ ክፍለ ከተማ ደረጃቸውን የጠበቁና ሰው ተኮር ስራዎች መሰራታቸውን አይተናል ፦የተለያዩ የህበረሰብ ክፍል ተወካዮች

AMN ኅዳር -29/2017 ዓ.ም

በቦሌ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ደረጃቸውን የጠበቁና ሰው ተኮር ስራዎች መከናወናቸውን ማየታቸውንየተለያዩ የህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ተናገሩ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣የባህል መሪዎች፣የማህበራዊ ሚዲያና የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪ ተወካዮች በቦሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ጎብኚዎች እንደገለፁት በክፍለ ከተማው የተሰሩ የልማት ስራዎች ሰው ተኮር መሆናቸው አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን እንደሚጡም ተናግረዋል።

የቦሌ ክፈለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አለምፀሀይ ሽፈራው በጉብኝቱ ላይ እንደገለፁት ልማቶች በማህብሰቡና በተቋማት ተሳትፎና በክፍለ ከተማው አቅም የተገነቡ ናቸው።

በከተማዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከፍለ ከተማው የመሠረተ ልማት ግንባታ ደረጃው የጠበቀ ማራኪ እንዲሆን አስችሎታልም ብለዋል።

ለዚህም የማህብሰቡ፣ የተቋማት ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ በማስተባበር እረገድ የኮር አመራሮች ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የመሠረተ ልማቶቹ በህገወጥ መሬት ወረራ የተገነቡ የሸራ ቤቶች ገፅታ የቀየረ፣ህገወጥ የንግድ ስፍራዎች የነበሩ እና ጨለማ በመሆናቸው ህብረተሰቡን ለዘረፋና ጥቃት ያጋልጡ እንደነበረ ገልጸዋል።

እነዚህን ስፍራዎች በአገባቡ በማልማት ለህዝብ አገልገሎት እንዲውሉ እና የሥራ እድል እንዲፈጥሩ ከመደረጉም በላይ ንፁህ ፅዱና ብርሃናማ በማድረግ የፀጥታ ስጋትነታቸውን የቀረፈ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በጉብኚቱም የስፖርት ሜዳዎች፣ ፓርኮች፣ የመንገድ አካፋዮች፣የህጻናት መጫወቻዎች የመንገድ እና የድልድይ መሠረተ ልማት ግንባታዎች መጎብኘታቸው ታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ክፍለ ከተማው ለተቋማት ግንባታ ልዩ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።

መድረኩን የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review