AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም
በታክስ ኦዲት የሚወሰኑ ውሳኔዎችን ጥራት የሚያረጋግጥ አዲስ የስራ ክፍል አደራጅቶ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
ቢሮው ይህን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል ፡፡
አዲሱ የታክስ ኦዲት ጥራት አረጋጋጭ የስራ ክፍል ከዚህ በፊት በታክስ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን የሚያረጋግጥ ባለመኖሩ ይፈጠሩ የነበሩ ክፍተቶችንና ብልሹ አሰራሮችን የሚያስቀር ስለመሆኑም ተገልፃል ፡፡
አዲስ የተደራጀው የስራ ክፍል በአገልጋዩና ተገልጋዩ መካከል ያለውን ታማኝነት የሚያረጋግጥና የስራ ክፍሉ አግባብነት የሌላቸው የኦዲት ውሳኔዎችን እንዲታረሙ የሚያስችል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
የተደራጀው የስራ ክፍል ተጠሪነቱ በቀጥታ ለቢሮ ሀላፊው ስለመሆኑም ለማወቅ ተችሏል ፡፡
በፅዮን ማሞ