በትላንትናው እለት የተመረቁትና በገላን ጉራ የሚገኙት ሶስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ጀመሩ

You are currently viewing በትላንትናው እለት የተመረቁትና በገላን ጉራ የሚገኙት ሶስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ጀመሩ

AMN-ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በትላንትናው እለት በተመረቁትና በገላን ጉራ በሚገኙት ሶስት ትምህርት ቤቶች በመገኘት የመማር ማስተማር ስራውን አስጀምረዋል።

ሀላፊው ለተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተማሪዎች ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ሆነው በተገነቡት ትምህርት ቤቶች እየተማሩ የላቀ ውጤት ለማምጣት እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችና ሌሎች አመራሮች መገኘታቸውን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review