AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም
አደጋው ከደረሰባቸው 18 ሰዎች መካከል ሶስቱ ከባድ ጉዳት ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል አንድ ህፃን ይገኝበታል ተብሏል፡፡
መነሻንውን ሚኒያፖሊስ ያደረገው አውሮፕላኑ 80 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ነው፡፡
አደጋው የደረሰው አውሮፕላኑ ቶሮንቶ በሚገኘው ፒርሰን አየር ማረፍያ ለማረፍ ሲል በድንገት በመገልበጡ ነው፡፡
ቶሮንቶ ከሰሞኑ ከባድ ንፋስ የቀላቀለ የአየር ሁኔታ እያስቸገራት እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የካናዳ ባለሥልጣናትም የአደጋው መንስኤ ላይ ምርመራ ይካሄዳል ማለታቸወን ሬውተርስ ነው የዘገበው፡፡