AMN-ታህሣሥ 26/2017 ዓ.ም
በአሁኑ ወቅት የሶማሌ ክልል ዓመታዊ የእንቁላል ምርት ግምት 56 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ።
በጂግጂጋ ከተማ ብሔራዊዉን የሌማት ትሩፋት ሥራ በትጋት እየተገበረ ያለው የሆርን አፍሪክ የዶሮ ርባታ ማዕከል 52000 ዶሮዎች በማርባት 35000 እንቁላሎችን በቀን እያመረተ ይገኛል።
ሀገር አቀፉ ንቅናቄ ከመጀመሩ አስቀድሞ አጠቃላይ የክልሉ አመታዊ የእንቁላል ምርት 3.5 ሚሊዮን እንደነበር ተመልክቷል ።
በአሁኑ ወቅት ያለው የክልሉ አመታዊ የእንቁላል የምርት ግምት 56 ሚሊዮን መድረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።