በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ 242 ሺ በላይ ሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዱ ነው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ 242 ሺ በላይ ሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዱ ነው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

AMN – ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ 242 ሺ በላይ ሰልጣኞች ተመዝግበው ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የኢትዮጵያ ወጣቶች ተገቢ እና ለዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂና የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ የተቀረጸ ፕሮግራም ነው፡፡

መርሐግብሩ ሁሉንም ተደራሽ ለማድረግ ማንኛውም ሰው ባለበት ሆኖ ስልጠና መውሰድ እንዲችል ተደርጎ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም በርካቶች በእድሉ እየተጠቀሙ መሆኑን በማንሳት ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሶስት ወራት ከ 242 ሺ በላይ ሰልጣኞች ተመዝግበው ስልጠናውን እየወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ለስልጠናው በአጠቃላይ ከተመዘገቡት ውስጥ ከ 81 ሺ በላይ የሚሆኑት መሰረታዊ ፕሮግራሚንግ ስልጠና እየተከታተሉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከ 78 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ መሰረታዊ የዳታ አናሊስስ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ከ 82 ሺ በላይ የሚሆኑት መሰረታዊ የአንድሮይድ አፕሊኬሽን ስልጠናዎችን እየወሰዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የነጻ የስልጠና እድሉ በኦንላይን የሚሰጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የእውቅና ሰርተፍኬት የሚያሰጥ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና በተለያየ መስክ ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰብ ክፍሎች በዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰፊና ሁሴን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review