AMN – የካቲት 16/2017 ዓ.ም
በቤኒሻንጉል ጉሙዝክ ክልል አሶሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
በኮንፈረንሱ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የአመራር አካላት ተገኝተዋል።
ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰቡ ክፍሎች በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።