በአነፍናፊ ውሻ የታገዙ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከል የሚያስችል የቁጥጥር ማዕከል ሥራ ጀመረ

You are currently viewing በአነፍናፊ ውሻ የታገዙ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከል የሚያስችል የቁጥጥር ማዕከል ሥራ ጀመረ

AMN – ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የዱር እስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ በአነፍናፊ ውሻ (CANINE UNIT) የታገዙ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ዝውውር ለመከላከልና የቁጥጥር ስራዎችን ለማከናወን የሚያግዝ ልዩ የቁጥጥር ማዕከል ሥራ ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ የዱር እስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እና በአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን የቴክኒክ ድጋፍ የተቋቋመው ልዩ የቁጥጥር ማዕከል በቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስትር አማባሳደር ናሲሴ ጫሊ ፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጂራ ፣ የአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review