AMN- ጥቅምት 13/2017 አ.ም
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ሲል በሚደረገው ጨዋታ በባርሴሎና በኩል ግብ ጠባቂው አንድሬ ቴርስ ቴገን በነበረበት የቆየ ጉዳት የማይሰለፍ ሲሆን ፤ ፌራን ቶሬስ፤ አንድሬስ ክሪስቴንሰን፤ ሮናልድ አራሆ እና ማርክ በርናል ወደሜዳ አይገቡም፡፡
ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም ያደረጓቸውን 13 ጨዋታዎች ፤ 9ኙን ባየር ሙኒክ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲወስድ በ3ቱ ባርሴሎና አሸንፎ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡
አርቢ ላይብዚሽ ከሊቨርፑል ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡
በሬድ ቡል አሬና በሚደረገው ጨዋታ በአርቢ ላይብዚሽ በኩል ደቪድ ራውም፤ ኒኮላስ ስዋልድ እና ቫቪየር ሽላገር አይሰለፉም፡፡
በቀዮቹ በኩል ግብ ጠባቂው አሊሰን ቤከር እና ሃርቬይ ኤሊዮት ከጨዋታ ውጭ ሲሆኑ፤ የዲያጎ ዦታ እና ፌዴሪኮ ኬዛ የመሰለፍ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡
የቀዮቹ አሰልጣኝ አርን ስሎት ኬዛ ለረጅም ጊዜ ነው የፈረመው፤ ለክለቡ የሚያበረክተውን አስተፅኦ ወደፊት እናያለን፤ ከጣልያን ሴሪ አ እንደመምጣቱ መጠን የፕሪምየር ሊጉ አጨዋወት ፈተና እንደሚሆንበት ይታመናል ነው ያሉት፡፡
በሌሎች ጨዋታዎ ማንችስተር ሲቲ ከስፓርታ ፕራግ ፤ ያንግ ቦይስ ከኢንተር ሚላን ፤ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሊል፤ ፤ ቤነፊካ ከፌኔርባቼ፤ ሬድቡል ሳልስበርግ ከ ዳይናሞ ዛግሬቭ የዛሬ ምሽት 4 ሰዓት መርሃ ግብሮች ናቸው፡፡
አታላንታ ከሴልቲክ እና ብሬስት ከባየር ሌቨርኩሰን 1 ሰዓት ከ45 ሲል ይጀምራሉ፡፡
በሙሉቀን ጌትነት