AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ 1(ለ)ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ እንዳስታወቀው በ2016 በጀት አመት በዕፅ ዝውውር ከደረሱ ጥቆማዎች መካከል ጠቅላይ መምሪያው የምርመራ መዝገቦችን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አጣርቶ ለዓቃቤ ሕግ ከላከው መዝገቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸው ብሎ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው፡-
1. ሚ/ር ቺቡኬ ዳንኤል፡- 12 አመት ፅኑ አስራት እና 4,000 ብር መቀጮ፣
2. ሚ/ር ኢጎር ዲማቶስ ዱትራ፡-3 አመት ከ9 ወር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
3. ሚ/ር ሉዊስ ሚጎል ኮናሮጂ፡- 4 አመት ፅኑ አስራት እና 4,000 ብር መቀጮ ፣
4. ሚ/ር ኬብሮም ሙንዲሀኪ ፡- 4 አመት ፅኑ አስራት እና 2,000 ብር መቀጮ፣
5. ሚ/ር ሳንጀብ ሙክርጂ ፡-6 አመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እና 7,000 ብርመቀጮ፣
6. ሚ/ር ሚስ ጊርሊዬ አሚ፡- 3 አመት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
7. ሚስ ሄልቪ አልቫላ ፡- 5 አመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
8. ራሄል ለገሰ ፡-3 አመት ፅኑ አስራት 3,000ብር መቀጮ፣
9. ተስፋነሽ አለንሳ፡- 3 አመት ብር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ ፣
10. ሚስስ ፑርናማ ጊታ፡- 15 አመት ብር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
11. ሚስ ናፈትፓት ኑአመንሮም፡- 4 አመት ከ 5 ወር ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
12. ሚስ ዚቱየትነህ፡- 5 አመት ፅኑ አስራት እና በብር 3,000 ብር መቀጮ፣
13. ሚ/ር ማርክ ፖወሊኮወ፡-5 አመት ከ 6 ወር ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
14. ሚ/ር ኢማኑኤል ኡዙቸክው፡-6 አመት ፅኑ አስራት እና 8,000 ብር መቀጮ፣
15. ባህሩ ወልዴ፡- 12 አመት ፅኑ አስራት፣
16. ሚ/ር አስዋልደረፋይል ሄርና፡- 4 አመት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ ፣
17. ታምሩ ፍቅሬ፡- 12 ዓመት ፅኑ አስራት እና 4,0000 ብር መቀጮ፣
18. ግሬስ አዋርድር፡- 2 አመት ከ9 ወር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
19. ሚስ ዜመዬ አዩን፡- 5 አመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
20. ሚ/ር ሞሀመድ ሳሉሞኪላማ፡- 6 አመት ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
21. ሚ/ር ሩአንደርሰደ ሰመዝ፡- 3 አመት እስራት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
22. ሚ/ር አሊዬ አቡዋ፡-4 አመት ፅኑ አስራት እና 2000 ብር መቀጮ፣
23. ሚስ ቻኒካን ቡናሙኤን፡- 3 አመት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
24. ሚስስ ቱርናማ ጊታ ሳሪ፡-4 ዓመት ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ ናቸው።
የተያዙ ኢግዚቢቶች በአይነት እና በመጠን በአጠቃላይ 176,881.61ግራ ምኮኬን፣ 924,450 ግራም ካናቢስ፣ 32,100.89 ግራም ሄሮይን፣ 5,089 ግራም ሄሮይን እና ሞርፊም መሆናቸው ታውቋል።
ግለሰቦቹ ዕፁን ለማዘዋወር የሚጠቀሙባቸው መንገዶች በሆድ/በሰው አካል ውስጥ/ በማህፀን/ ኮንዶም በመጠቀም፣ በሻንጣ ውስጥ፣ በጫማ ሶል፣ ወፍራም ልብስ በማስመሰል በመልበስ፣ በተለያየ የመኪና አካል ውስጥ፣ በሻንጣ መጎተቻ ብረት ውስጥ በመበየድ እንደሆነ የወንጀል ምርመራ ቡድኑ አረጋግጧል።
የዕፅ የአዘዋዋሪዎቹ ሀገራት:- ናይጀሪያ፣ ኢትዮጵ፣ ብራዚል፣ ታይላንድ፣ አንጎላ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቪንዞላ፣ ቢኒን፣ ካሜሮን፣ ናሚቢያ፣ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ቦሊቪያ፣ ፖላንድ፣ ጀርመን፣ ሴንትራል አፍሪካ፣ ህንድ፣ ቱኒዚያ፣ ኢንዶኒዥያ፣ ማላዊ፣ ጅቡቲ፣ ካናዳ፣ ሞዛምቢክ እና ቱርክዬ መሆኑ ታውቋል።
የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋወሪዎቹ መነሻ ብራዚል (ሳኦፖውሎ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ)፣ አዲስ አበባ፣ አንጎላ ታንዛኒያ፣ ኬኒያ እና ሌሎች ሀገራት ሲሆን መዳረሻቸው ደግሞ ናጀሪያ (ሌጎስ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ)፣ ህንድ፣ ዱባይ፣ አዲስ አበባ እና ታይላንድ ናቸው።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት 24 የምርመራ መዝገቦችን መርምሮ በሕግ የተከለከሉ ዕጾችን የማዘዋወር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾችን ያርማል፤ ሌሎችን ያስተምራል በማለት ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ከ2 ሺህ ብር እስከ 8000 ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖባቸዋል።
በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት ላይም ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመረጃው አስታውቋል።