በአዲስ አበባ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ትናንት ምሽት ተሰማ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ትናንት ምሽት ተሰማ

AMN-ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ትናንት ምሽት ተሰምቷል፡፡

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ አረጋግጠዋል።

ትናተት ምሽት 5፡11 ደቂቃ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ አረጋግጠዋል።

በአካባቢው ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴው አሁንም እንዳልቆመም ዶክተር ኤሊያስ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review