በአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን ስራ እየተሰራ ነው-አቶ አህመድ ሽዴ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን ስራ እየተሰራ ነው-አቶ አህመድ ሽዴ

AMN – ታኀሣሥ 19/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን ስራ እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በመዲናዋ የተገነቡ የልማት ሥራዎችን በጎበኙበት ወቅት፣ በከተማዋ እየተሰራ ያለው የልማት ስራ እጅግ ግዙፍ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይም በመዲናዋ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደገ እና ዘመናዊና ለስራ ምቹ ከተማን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡

አረንጓዴ እና ሰፋፊ መንገዶች ለዘመናዊ ከተማ ግንባታ እና ለትውልድ የሚሸጋገሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ሰፊ የልማት ውጤት ያመጣ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሚኒስትሩ በተመለከቱት የገላን ጉራ መንደር አንድ ማህበረሰብ ዘመናዊ ኑሮ የሚያኖረው መሰረተልማት መሟላቱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ነዋሪዎቹ ከበፊቱ ህይወታቸው የተሻለ አኗኗር በማግኘታቸው መደሰታቸውን መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የተመለከቱት ልማት ፍጥነት ብቻ ሳይሆን ጥራትን ያገናዘበ እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ልማቱ በአመራር ቁርጠኝነት፣ በእውቀት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመናበብ እየተሰራ መሆኑን መመልከታቸውንም ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review