በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የሰራዊት ቀን በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ/ም የኢፌዲሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በክብር እንግድነት በተገኙበት ፣ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና በርካታ ህዝብ የታደመበት 116ኛ ዓመት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆየቶ የማጠቃለያ ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ በወታደራዊ ትርኢቶችና ሰልፎች በድመቀት ተከብሯል፡፡
«በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሰራዊት» በሚል መሪቃል የተከበረው የሰራዊቱ ቀን የሀገር መከላከያ ብዝሃነትንና አብሮነትን ባንፀባረቀ፣ ለውስጥ ሆነ ለውጭ ጠላቶች ሰራዊቱ ህዝቡንና ሀገርን የመጠበቅ ብቃቱን ባረጋገጠ ሁኔታ በተከበረው ፕሮግራም ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ አካላት አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በዓሉ በሚከበር ወቅት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ዝግጅቱ በመጠናቀቁ መንገዶች የተለመደ አገልገሎታቸውን መስጠት መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረሃይል ስም ለመላው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና አባላት በድጋሚ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ