AMN ህዳር 19/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የቅንጅታዊ አሰራር አፈፃፀምን በተመለከተ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ የከተማው ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በመድረኩ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ ከ20 ሴክተሮች ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ በተለያዩ ዘርፎች ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል።
አዲስ አበባ በተፈጥሮ የታደለች ለመሆኑ በውስጧ ያሉ በርካታ ወንዞች ማሳያ መሆናቸው የተነሳ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት የቆሻሻ ማስወገጃ የነበሩ ወንዞች በበጀት ዓመቱ በተሰሩ ስራዎች ወደ አረንጓዴ ልማት ተቀይረው አማራጭ የመዝናኛ ስፍራ መሆናቸውም ተጠቁሟል።
ቢሮው አረንጓዴ ልማት ከማስፋትም በተጨማሪ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ በተለይ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመተባበር በለሙ ስፍራዎች ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ ስለመቻሉም ተጠቁሟል፡፡
በራሄል አበበ