በአዲስ አበባ ከተማ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን የኑሮ ጫና ለማቃለል እየተሰራ ነው፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህልን በማዳበር ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን የኑሮ ጫና ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት በአዲስ አበባ ከተማ ከማዕከል እስከ ወረዳ

ከ400ሺ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች ማዕድ ማጋራት ተካሂዷል።

በከንቲባ ጽህፈት ቤት ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ያጋሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ እና አቅመ ደካማ የሆኑ ነዋሪዎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንዲደገፉ እና የኑሮ ጫናቸው እንዲቃለል እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸው በአልን በደስታ እንዲያሳልፉ ለማድረግ የተለያዩ ባለሀብቶችንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር መከናወኑን ገልጸዋል።

በአሉን በማስመልከት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች የማስተላለፍ ተግባር እንደሚከናወንም አስታውቀዋል።

አቅመ ደካሞችና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ነዋሪዎችን የኑሮ ጫና ለማቅለል የሚከናወነው ተግባር በመንግስት በጀት ብቻ የሚሸፈን ባለመሆኑ የተለያዩ በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች በበጎ ስራው ለተባበሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review