በአዲስ አበባ ከተማ ትውልድ ግንባታ ላይ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶች የትውልዱ የስበት ማዕከል ሆነዋል – ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ ትውልድ ግንባታ ላይ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶች የትውልዱ የስበት ማዕከል ሆነዋል – ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ትውልድ ግንባታ ላይ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶች የትውልዱ የስበት ማዕከል መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኃላፊው ከከተማና ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በየካ ክፍለ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የትምህርት ቤቶችን ማስፋፊያ ጎበኝተዋል።

በክፍለ ከተማው እየተገነቡ ያሉት ተጨማሪ የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያዎች ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ለትምህርት ማህበረሰቡ ምቹ ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ኃላፊው ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ትውልድ ግንባታ ላይ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶች የትውልዱ የስበት ማዕከል ስለመሆናቸው የገለፁት ሀላፊው፣ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚሰራው ትምህርት ቤት በመሆኑ በቀጣይም ቢሯቸው ከባለድርሻዎች ጋር በመሆን የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚታትርም አንስተዋል፡፡

በጽዮን ማሞ

+3

All reactions:

69You and 68 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review