በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ ላቀረቡ አመልካቾች አገልግሎቱ ከህዳር 1 ጀምሮ ይሰጣል-የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ ላቀረቡ አመልካቾች አገልግሎቱ ከህዳር 1 ጀምሮ ይሰጣል-የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

AMN – ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ የክፍለሃገር መሸኛ አስገብተው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተገልጋዮች ያቀረቡትን መረጃ የማጥራት ሂደት ማጠናቀቁን የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱን ከህዳር 1 ጀምሮ ለመጀመር ዝግጅት መደረጉንም ኤጀንሲው ገልጿል።

በመሆኑም ከነገ ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ጀምሮ በነዋሪነት ለመመዝገብ ያመለከቱ ተገልጋዮች የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት የወረዳ ጽ/ቤት እስከ ጥቅምት 22 ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

ተገልጋዮች የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅና ምዝገባው በኤጀንሲው ጽ/ቤት የሚከናወን በመሆኑ የክፍለሃገር መልቀቅያ ባስገቡበት ወቅት ከጽ/ቤቱ የተሰጣቸውን ማስረጃ ይዘው እንዲቀርቡም ተጠይቋል፡፡

በዚህ የማጥራት ሂደት ያላለፈ አመልካች በነዋሪነት ተመዝግቦ አገልግሎት ማግኘት የማይችል በመሆኑ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዘውትር ከሰኞ እስከ እሁድ ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሳስቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review