በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የተሻለ ስራ እንድንሰራ መነሳሳትን ፈጥሮልናል – የሐረር ከተማ አስተዳደር ልዑካን

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የተሻለ ስራ እንድንሰራ መነሳሳትን ፈጥሮልናል – የሐረር ከተማ አስተዳደር ልዑካን

AMN – ሚያዝያ 01/2017

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ በሚገኙ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች መደሰታቸዉን የሐረር ከተማ አስተዳደር ልዑካን ተናገሩ፡፡

የሐረር ከተማ አስተዳደር ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ በአረንጓዴ መሠረተ ልማት ስራዎች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ጉብኝት አጠናቋል፡፡

በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤሊያስ የኒስ የተመራዉ ቡድን የህዝብ መዝናኛ በቦታዎችን ፡የችግኝ ጣቢያዎችን፡ የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ስራዎች እንዲሁም አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጨምሮ በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር የአረንጓዴ መሠረተ ልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

በልምድ ልውውጡ የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ አለሙ : የቢሮው አማካሪ አቶ ነጋሽ አረጋን ጨምሮ ሌሎች የቢሮዉ ባለሙያዎች ተገኝተው ስራዎችን በዝርዝር አስረድተዋል ።

በከተማዋ የተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች በእጅጉ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት የሐረርማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤሊያስ የኒስ በጉብኝቱ የአገኝቱን ተሞክሮ በመቀመር የተሻለ ስራ ለመስራት ከፍተኛ መነሳሳት እንደ ፈጠረላቸው መግፃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review