በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ፍጥነት፣ ጥራት እና የሀብት አጠቃቀም የሚደነቅ ነው- አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ፍጥነት፣ ጥራት እና የሀብት አጠቃቀም የሚደነቅ ነው- አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ፍጥነት፣ ጥራት እና የሀብት አጠቃቀም የሚደነቅ ስለመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ገለፁ፡፡

ከምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን በከተማዋ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን የጎበኙት አፈ ጉባኤዋ ሀብትን እና ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም በከተማዋ የሚታየው የፕሮጀክቶች አፈፃጸም አጥጋቢ እና የሚበረታታ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

ይህ የከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክት አፈጻፀም አቅምም ለእኛ የምክር ቤት አባላት ጭምር አራዓያ የሆነ ነውም ብለዋል፡፡

በከተማዋ እየተከናወነ ያለው ልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ታች ድረስ በመውረድ መመልከታቸውን የተናገሩት አፈጉባኤዋ በመልሶ ማልማት እየተገነቡ ያሉ አካባቢዎች የግንባታ ሂደትም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አባላት የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ የጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደር፣ የኮሪደር ልማት እና አዲስ ኢንተርናሽናል ኤግዚብሽንና ኮንቬንሽን ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በአሰግድ ኪ/ማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review