በአዲስ አበባ ከተማ የተደራጀው የሰላም ሰራዊት የሰላም አርበኝነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ የተደራጀው የሰላም ሰራዊት የሰላም አርበኝነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል

AMN- መስከረም 7/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች፤ ወረዳዎችና ቀጠናዎች የተደራጀው የሰላም ሰራዊት የሰላም አርበኝነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በመጪዎቹ ሳምንታት የሚከበሩት ኃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የሰላም ሰራዊቱና የፀጥታ ኃይሎች ብርድና ዝናብ ሳይበግራቸው የአከባቢያቸውን ሰላም በ ንቃት በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመዘዋወር ጎብኝተዋል፡፡

የቢሮ ሃላፊዋ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በመገኘት በስምሪት ላይ የሚገኙትን የፀጥታ ሃይሎች እንቅስቃሴ በማየት ካበረታቱ በኋላ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መስጠታቸውን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review