AMN – ህዳር 2/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከልና ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች የወንጀል ድርጊት በ37 በመቶ መቀነሱን የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናገሩ ::
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ስራዎችን እየገመገሙ ነዉ ::
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የከተማዋን ሰላም እና ፀጥታ ለማጽናት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል::
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ የወንጀል ድርጊትን ቀድሞ ለመከላከልና ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች የወንጀል ድርጊት በ37 በመቶ ቀንሷል ብለዋል::
በሩብ ዓመቱ በመዲናዋ የተከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት እሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ በድምቀት መከበራቸዉንም ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ በሩብ ዓመቱ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ስብስባዎችም ማስተናገዷን አንስተዋል::
የሰላም እና ፀጥታ ስራን ለማጠናከር በሩብ አምቱ 22 ሺህ የሰላም ሰራዊቶች ሰልጥነዉ ወደ ስራ መግባታቸውንም ገልጸዋል::
ህገወጥ የመሬት ወረራ፣ ህገወጥ የመንገድ ላይ ንግድና ሌሎች የደምብ መተላለፍ ችግሮች መቀንሳቸዉንም ነው ኃላፊዋ የተናገሩት::
በቴዎድሮስ ይሳ