በአዲስ አበባ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ

AMN-ታህሣሥ 21/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።

ክትባቱ ከታህሳስ 21 እስከ 25 ድረስ ከ9 እስከ 14 ዓመት ላሉ ታዳጊ ሴት ህፃናት በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ተነግሯል።

በመስከረም አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት በነበረው የክትባት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ በአገራችን ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በገዳይነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠውን የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል ክትባት መሰጠቱ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በዚህ ክትባት ከ 177 ሺህ በላይ በተጠቀሰው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴት ታዳጊዎችን ለመከተብ መታቀዱንም አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱም በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ይህንን ክትባት ጠቀሜታዉን በመረዳት ወላጆች ኅላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ክትባቱ በዘመቻ ብቻ ሳይሆን እንደ መደበኛ ክትባት እንደሚቀጥልም ተነግሯል።

በትዕግሥት መንግሥቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review