በአዲስ አበባ የተተገበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም በተሞክሮነት የሚወሰድ ነው- የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች

You are currently viewing በአዲስ አበባ የተተገበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም በተሞክሮነት የሚወሰድ ነው- የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የተተገበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም ለሌሎች ክልሎች በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ፡፡

አመራሮቹ ነገ የሚጀመረውን ሁለተኛውን የብልፅግና መደበኛ ጉባኤ በማስመልከት ባለፉት የለውጥ አመታት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በለሚ እንጀራ ማዕከል ጉብኝታቸው የታዘቡትን ሲናገሩ፣ ከጤፍ አምራቹ አርሶ አደር ጀምሮ እንጀራውን ከሚጋግሩ እናቶች እስከ ነጋዴው ብሎም እስከ ተጠቃሚው ሸማች ሁሉንም ያስተሳሰረ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ማዕከል ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ዋና ዋና መግቢያ በሮች ገንብቶ ወደ ስራ ያስገባቸው የግብርና ምርቶች የግብይት ማዕከላት የከተማ ነዋሪውን ብቻ ሳይሆን አርሶ አደሩን፤ የፋብሪካ ባለቤቶችን፤ የፋይናንስ ተቋማትንና ነጋዴውንም ጭምር የሚያስተሳስር መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ናቸው፡፡

ይህም ለሁሉም ክልሎች ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዘርፈ ብዙ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ስኬት ለሁሉም ክልሎች በእርሾነት እያገለገለ የሚገኝና የኢትዮጵያን ብልጽግና አይቀሬነት ያረጋገጠ ስለመሆኑ የተናገሩት የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ናቸው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ለህዝብ የገባውን ቃል በመሬት ላይ በማውረድ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን መመልከታቸውን አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡

እነዚህን በአዲስ አበባ የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን ይበልጥ ለማስፋፋት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አመራሮቹ አስታውቀዋል፡፡

በምትኩ ተሾመ

+2

All reactions:

138Asmare Gashu and 137 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review