በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትና ፍትሀዊነትን ያረጋገጡ ናቸው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትና ፍትሀዊነትን ያረጋገጡ ናቸው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የልማት ስራዎች በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የብልፅግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስጎብኝተዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎች ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ የሚዘልቀውን 21 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ የግንፍሌ አካባቢ 19 ነጥብ 5 ኪሜ የሚሸፍን ወንዝ ዳርቻ ልማት ፣የካዛንቺስን መልሶ ማልማት ፤ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና 40 ነጥብ 4 ኪ ሜ የሚሸፍን ኮሪደር ልማት እንዲሁም የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ገላን ጉራ የተቀናጀ የልማት መንደር እና የአካበባቢ ልማት ፤ የፒያሳ ልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶች መኖሪያ መንደር ፤ የቦሌ ቡልቡላ ካርጎ ተርሚናል እና የአቃቂ አዲሱ መንገድ የ37 ኪ.ሜ የአረንጓዴ ልማት ሥራ ፤ “የብርሃን አዳሪ ት/ቤት” እና የ “ለነገዋ” የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በብልፅግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መጎብኘታቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አመልክተዋል።

የከተማችን መሠረተ ልማት አቅርቦት እና ቅንጅት በፍጥነት እያደገ ያለ መሆኑንና ከተማዋን ፅዱና ዉብ በማድረግ ገፅታዋን እየቀየረ ያለ ልማት ነው ።

በከተማዋ የተገነቡት መሰረተ ልማቶቹ ፣ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትና ፍትሀዊነትን ያረጋገጡ ናቸው።

በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የተጎበኙት ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎች ብልፅግና ከባለፈው ጉባኤ ወዲህ በቃሉ መሰረት አዲስ አበባን ዉብ አበባ ለማድረግ የተገበራቸው ሥራዎች አካል መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review