በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ ሁለት ማዕከላት ለ3ኛ ወገን ተላለፉ
AMN – ሀምሌ 5/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ ሁለት የገበያ ማእከላትን የአስተዳደር ስራዎች አውት ሶርስ በማድረግ ለ3ተኛ ወገን አስተላለፈ።
ቢሮው የኮልፌና ለሚኩራ የገበያ ማዕከላትን የአስተዳደር፣ የጽዳትና የጥበቃ ስራዎችእንዲሰሩ ነው ለሁለት የግል ድርጅቶች ያስተላለፈው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የገበያ ማእከላት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲቀርብ ለማድረግ ነው የአስተዳደር ስራዎችን አውትሶርስ በማድረግ ለ3ተኛ ወገን እንዲተላለፍ የተደረገው ብለዋል።
ሀብ ቢዝነስ ግሩፕ የአስተዳደሩን ስራ የያዘ ሲሆን ኢትዮ ጥበቃ ደግም የጽዳትና የጥበቃ ስራውን እንዲሰሩ የተመረጡ ድርጅቶች ናቸው ብለዋል።
ድርጅቶቹ ከሐምሌ 1 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ወደስራ መግባታቸውም ተገልጿል።
የግብይት ስርዓቱ በየሳምንቱ ንግድ ቢሮ በሚያወጣው ተመን የሚካሄድ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን አጠቃላይ ሂደቱን ቢሮው እንደሚቆጣጠርም ታውቋል ።
ሄለን ጀንበሬ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!