በአዲስ አበባ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ በለጸገ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ በለጸገ

AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

ቴክኖሎጂው ተግባራዊ ሲደረግ በከተማው የትራፊክ መጨናነቅ በሚታይባቸው መንገዶች ከሰው ንኪኪ ነፃ በሆነ መልኩ መረጃዎች በመቀበል አመራጭ መንገዶችን በመጠቀም የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ ያስችላል ተብሏል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር በቴክኖሎጂ በሚደገፍበት ሁኔታ ላይ ከጉባ ቴክኖሎጂ ስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በከተማው የሚታየውን የትራፊክ ቁጥጥር ለማገዝ በጉባ ቴክኖሎጂ አማካይነት የበለፀገ ሲስተም ቀርቦ የተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች በተኙበት ግምገማ እንደተደረገበት ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በከተማው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቅረፍ የተሽከርካሪን ምልልስ በመጨመር የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እንዲቻል የትራንስፖርት ቁጥጥር በቴክኖሎጂ መደገፍ እንዳለበት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

የጉባ ቴክኖሎጂ ማርኬቲግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሚሊዮን ታምሬ፤ ቴክኖሎጂው ተግባራዊ ሲደረግ በከተማው የትራፊክ መጨናነቅ በሚታይባቸው መንገዶች ከሰው ንኪኪ ነፃ በሆነ መልኩ መረጃዎች በመቀበል አመራጭ መንገዶችን በመጠቀም የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review