በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ

AMN – ሰኔ 4/2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በ182 የመፈተኛ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት መሰጠት ጀምሯል።

ዛሬ ሰኔ 4 እና ነገ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የሁለተኛ ደረጃ መግቢያ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሁሉም የመንግሥት እና የግል እንዲሁም የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እየወሰዱ ነው።

የዘንድሮ የአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ብዛት 86 ሺህ 672 እንደሆነ ከትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

በፈተናው ሂደት ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲሠሩ እና ከኩረጃ በጸዳ መልኩ እንዲፈተኑ በፈታኝ መምህራን፣ በሱፐርቫይዘሮች እና በትምህርት አመራሮች አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ኤኤምኤን ምልከታ ባደረገባቸው የአራዳ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የመፈተኛ ጣቢያዎች ለማረጋገጥ ችሏል።

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ እና ነገ የሚሰጥ ሲሆን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ደግሞ በቀጣዩ ሳምንት ከሰኔ 12 እስከ 14 እንደሚሰጥ ከወጣው መርሐ-ግብር ለማወቅ ተችሏል።

በምትኩ ተሾመ

#Addisababa

#Ethiopia

#AMN

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review