በአዲስ አበባ 11 ሺ የሰላም ሰራዊት አባላት ተመረቁ

You are currently viewing በአዲስ አበባ 11 ሺ የሰላም ሰራዊት አባላት ተመረቁ

AMN-መስከረም 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን 11 ሺ የሰላም ሰራዊት አባላት አስመርቋል።

አባላቱ በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ የአካል ብቃትና ወታደራዊ ስልጠና እንደተሰጣቸው ተጠቁሟል።

በከተማዋ የሰላም ሰራዊት አባላት ስራ ከጀመሩበት ጊዜ ወዲህ የወንጀል ክስተት ምጣኔ መቀነሱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል።

ከተማዋ የአስተማማኝ ሰላም ባለቤት የሆነችው በሰላም ሰራዊቱ ፣ በፀጥታ ተቋማትና በነዋሪዎች ቅንጅት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ናቸው።

ተመራቂዎቹ የከተዋን ሰላም ዘላቂ የማድረግ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ኮሚሽነር ጌቱ አደራ ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በአምስት ዙር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በርካታ የሰላም ሰራዊት አባላት እንደሚሰለጥኑ ተጠቁሟል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review