በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚነሱ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል- የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

You are currently viewing በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚነሱ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል- የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚነሱ ቅሬታዎች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

የኤጀንሲው አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አገልጋይ በተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ በተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ለማ (ዶ/ር) በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎችን እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንደ ግብአት ወስዶ በአስቸኳይ እየፈቱ ማለፍ እና የተገልጋዮችን ዕርካታ ማረጋገጥ ለስኬታማ አፈጻጸም እንደሚያበቃ ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በተቋሙ በሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ህብረተሰቡም ሆነ የመዋቅሩ ሰራተኞች ያለባቸውን ችግሮች በመለየት እና ወርዶ በማወያየት በቀጣይ የመፍትሄ እርምጃዎች በጋራ እየወሰድን እንሄዳለን ሲሉ በአፅንኦት አብራርተዋል።

ከተነሱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች መካከል የሰራተኞች ጥቅማጥቅም በሰዓቱ አለመግዛት፣ የግብአቶች የጥራት መጓደል፣ ለዘርፉ ሰራተኞች የህክምና እና የትምህርት ዕድሎች፣ ከፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ሌሎችም በርካታ ሀሳቦች ቀርበው ተመክሮባቸዋል።

በሚዲያ ተቋሙ አማካኝነት ከተገልጋዮች የተነሱ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን የሚመለከተው ዳይሬክቶሬት የእቅዳቸው አካል አድርገው በአጭር ጊዚያት ውስጥ የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ በጋራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review